ሰበር ዜና
Tuesday, 08 September 2009
የመለስን ሥልጣን የመልቀቅ ጥያቄ ኢሕአዴግ ተቀበለ. መቼ?(በጋዜጣው ሪፖርተር)ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከወሳኝ የፓርቲ ስልጣንና የመንግሥት አመራር ለመልቀቅ ያቀረቡትን ጥያቄ ኢሕአዴግ በድምፅ ብልጫ ተቀበለ፡፡የመለስን ሥልጣን የመልቀቅ ጥያቄን ኢሕአዴግ ተቀበለ::
ጥያቄውን በመጀመሪያ ያስተናገደው የግንባሩ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሲሆን በጉዳዩ ላይ ሰፊ ክርክርና ውይይት በተካሄደበትና የሥራ አስፈፃሚው አባላት ለሁለት በተከፈሉበት በዚህ መድረክ አቶ መለስ ራሳቸው የተከራከሩበት ውይይት እንደነበር ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡ ጥያቄውን በመጀመሪያ ያስተናገደው የግንባሩ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሲሆን በጉዳዩ ላይ ሰፊ ክርክርና ውይይት በተካሄደበትና የሥራ አስፈፃሚው አባላት ለሁለት በተከፈሉበት በዚህ መድረክ አቶ መለስ ራሳቸው የተከራከሩበት ውይይት እንደነበር ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡”
Comment (ours):
እውነትም መቸ ነው መለስ ከስልጣን የሚወርደው? አሁን? ከ2002 (2010 GC) ምርጫ በሁውላ? ከ2007 (2015 GC) በሁውላ? መቸ….እስከመቸ? ነገሮችን በማድብስበስ በማጭበርበር ለሃያ አመት የቆየው የመለስ ዜናዊ መንግስት ዛሬ ከመቸውም ጊዜ በላይ በሃይል ካልሆነ በስተቀር በምንም መንገድ የሚለቅ አይመስልም። መለስ እራሱ በየጊዜው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እንደሚናገረው በጦርነት የተቆናጠጠውን በትረ-ሥልጣን ለመልቀቅ በህልሙም አያስበውም። በስልጣን ለመቆየትም በትግራይ ህዝብ ስም ይነግዳል። ዘርን ከዘር ያጨፋጭፋል። ይገድላል። ያስራል። አካል ያጎድላል። ይዘርፋል።…. ምኑ ተንግሮ ያልቃል?
ቁም ንገሩ ግን የመለስ ከስልጣን መውረድ አይደለም። ሌላ መለስ ከተተካ ምን ዋጋ አለው? የኢህአዴግ ከሥልጣን መውረድም አይደለም? ሌላ ቡድን፤ አገር ገንጣይ / አስገንጣይ፤ ዘረኛ መንግስት ከተተካ ምን ዋጋ አለው? የአገርን አንድነት በማስጠበቅ ሥበብም ህዝብን ረግጦ የሚገዛም አይደለም? ተመልስን ወደ ኃይለሥላሴ ወይም ወደ መንግስቱ ህይለማርያም ከሄድን ምን ዋጋ አለው?
ትግላችን በርግጥ መጀመሪያ ሃገርን የማዳን እና ልዑዋላዊነትን የማስክበር ነው። ነገር ግን መዳረሻችን መሆን ያለበት፤ በኢትዮጵያችን የግለሰብ እና የቡድን መብቶች ተከብረው፤ ስብአዊ መብታችን ሳይገሰስ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የእኛ በእኛ የተመረጠ መንግስት ማቆም ነው። ስለዚህ የመለስ መውረድም ሆነ መቆየት፤ ኢህአዴግ ስልጣን ላይ እስካለ ድረስ “ድስት ቢቀያየር ወጥ አያሳምርም” እንዲሉ ነው።
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
1 comment:
This is gimickery!
the only solution to this fachist government is - force! they have to be trashed, that might sober them up!
We will get our country!
My prayer is for Ginbot7 on behalf of the nation to privail by the lord almighty!
Post a Comment