Thursday, September 10, 2009

ዘመን-አራት ጎማ…እንቁጣጣሽ!

ዘመን ተሽከርክሮ- ዛቢያው ተንከባሎ፤
አዲስ ዓመት መጣ-ይኸውና ዞሮ።

አራት ጎማ አቁሞ-ዘመን ስም ሰይሞ
ሊገባ ነው ታየኝ- ማርቆስ ከበር ቆሞ።
ተነሳ ባርኔጣ- ማቴዎስ አክትሞ
ሉቃስ ይከተላል- ያድርስን ለከርሞ።

እንቁጣጣሽ ልበል- ራስ ካሳር ቆሜ
ሞያሌ ላለኸው- ለታላቅ ወንድሜ።
ጎንደር ለምትኖሩት-ወዳጅ ዘመዶቼ
በየክፍለ-ዓለሙ- ሁሉም ወገኖቼ
የቦራዊል ቆንጆ- ተወዳጅ እህቴ
የቡሮ ዱጊዋ-አንች ደግ አክስቴ
የአክሱሙ አድባር አባት-ግራዝማች አጎቴ
ሃሎ ወደ አስመራ- ደጃዝማች አያቴ
የጊምቢ ዋርካወች-እናትና አባቴ
ይድረስ በቦስጣ ቤት- እነሆኝ መልዕክቴ
መልካም አዲስ ዓመት-ይመኛል ልጃችሁ
በአንድነት በሰላም-ሁሌም ያኑራችሁ
ኢትዮጵያን አደራ-በአንድነት ይዛችሁ
ለሚመጣው ዓመት- ሰላም ያድርሳችሁ።

ዳግማዊ ዳዊት
መስከረም 2002
Ethio_dagmawi@yahoo.com

No comments: