Wednesday, February 10, 2010

ሿ ሿ ... ዳግም ምርጫ (የምርጫ ጭውውት ክፍል ሁለት)

ዳግማዊ ዳዊት
ethio_dagmawi@yahoo.com

ደሞ ምርጫ! ሿ ሿ ዳግም ምርጫ!
አንዋጋም ብለን … ካልን ሠላም ብቻ
እርስ በእርስ መናቆር … ሳናቆም ጥላቻ
ውስጣችን ሳይጠራ … አንቅረብ ለምርጫ!
እስኪ ሠላም ይውረድ! …
እስኪ ውስኪ እንራጭ! …
ካልቻልን አረንቻታ
ውስኪው ሠላም ይሁን- ፍቅር አረንቻታ!

ምርጫ ቦርዱ ቢለኝ … አልኩት አላውቀውም
ፍርድ ቤቱስ ሲለኝ … አልኩት አላምነውም
ሰብዓዊ-መብት ሲል … አልኩት አልታደልንም
መከላከያ ሲል … ነገርኩት እንዲል ዝም
ተቃዋሚወችስ ሲል … አልኩት አሳመሙኝ
እየተጣሉ አልኩት … ለምን ብሎ ቢለኝ
ፌደራል ሲጠይቅ … ለሞቴ ፈራሁኝ
ታድያ ዝግጅቱስ? ... አልኩት ምንም የለም
ማሸንፉስ ሲለኝ - እሱ አይታሰብም
ታድያ ትርፉስ ሲለኝ - አልኩት አላውቀውም።

ፏ! ፏ! ብሏል መለስ- ፏ! አለ እንጅ በሸገር
መተባበር ጠፍቶ …
መቻቻሉ ጠፍቶ
አገር ትቅደምቀርቶ
ቀና ማሰብ ቀርቶ … ደግ መስራት ለአገር
ህዝብ ማዳን ቀርቶ … ዘራፍ ማለት ለአገር!

ጠላት ቢደነፋም - ቢበዛ እንቅፋቱ
አይከፋንም ነበር - ለህዝብ መሞቱ
እናንት ሳትስማሙ - ገብታችሁ ለምርጫ
አይፈስም አልልም - የደም አረንቻታ።

ደሞ ምርጫ! ሿ ሿ ዳግም ምርጫ!
አንዋጋም ብለን … ካልን ሠላም ብቻ
እርስ በእርስ መናቆር … ሳናቆም ጥላቻ
ውስጣችን ሳይጠራ … አንቅረብ ለምርጫ!
እስኪ ሰላም ይውረድ! …
እስኪ ውስኪ እንራጭ! …
ካልቻልን አረንቻታ
ውስኪው ሰላም ይሁን - ፍቅር አረንቻታ!

እናንት ልብ ብትሉ - ግለኝነት ቀርቶ
አገር ማዳን ቢሆን - የዘንድሮው “ሞቶ”
ሕዝብ ማዳን ቢሆን - የዘንድሮው ጥረት
ለፍትህ ተታግልን - ለፍትህ ብንሞት
እንኳን አንድ መለስ - በህዝብ የተተፋ - የጋጠ-ወጥ አውራ
ገፍተን ባስወገድን - ግዙፉን ተራራ
ጣጥሰነው ገብተን …
ድሉን ተቀናጅተን …
በህዝብ ለህዝብ የቆመ - መሪያችንን መርጠን
ሠላም ብልፅግናን - ገንዝብ ባደረግን።

ደሞ ምርጫ! ሿ ሿ ዳግም ምርጫ!
አንዋጋም ብለን … ካልን ሰላም ብቻ
እርስ በእርስ መናቆር … ሳናቆም ጥላቻ
ውስጣችን ሳይጠራ … አንቅረብ ለምርጫ!
እስኪ ሰላም ይውረድ! …
እስኪ ውስኪ እንራጭ!…
ካልቻልን አረንቻታ
ውስኪው ሠላም ይሁን - ፍቅር አሪንቻታ!

No comments: