(Reported by Ethiopia Zare)
Saturday, 22 August 2009 18:14
‘ሌላው በአንድ ዓመቱ ታስሮ እየወጣ ልጄን አታስጨንቁት’ ወላጅ እናቱ
Ethiopia Zare (ቅዳሜ ነሐሴ 16 ቀን 2001 ዓ.ም. August 22, 2009)፦ የህወሓት መስራችና በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ውሰጥ ያለው አገዛዝ አውራ ናቸው የሚባሉት የአቦይ ስብሃት ነጋ የ13 ዓመት ታዳጊ ወጣት ልጅ ነሐሴ 10 ቀን 2001 ዓ.ም. ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ አዲስ አበባ ውስጥ ሁለት ሰዎችን በመኪና ገጭቷል።
የኢትየጵያ ዛሬ ምንጮች እንደገለጹት መንጃ ፈቃድም ሆነ መኪና የመያዝ ዕድሜው ያልደረሰው ይኸው ታዳጊ በጉርምስና ስሜት ሒልተን ሆቴል በራፍ ላይ ነው የመኪና አደጋውን ያደረሰው። በስፍራው የነበሩት የልጁ ወላጅ እናት “ይግጫ! ቢገጭ ምናለበት? ሌላው ሰው ገጭቶ በዓመቱ አይደል እንዴ የሚፈታው? ልጄን አታስጨንቁት!” ማለታቸውን የሰሙት እማኞች በእናቱ ድርጊት መበሳጨታቸውን ገልጸዋል።
የተገጪዎቹ ጉዳት ከፍተኛ ቢሆንም ጉዳዩ በሕግ እንዳይያዝ መደረጉንም ምንጮቻችን አክለው ገልጸዋል። ይሁን እንጂ አቦይ ስብሃት በልጃቸው ድርጊት በመበሳጨታቸው “ይታሰር! ይቀጣ!” ማለታቸው የተሰማ ቢሆንም፤ የተፈጸመውን የወንጀል ድርጊት የትራፊክ ፖሊስ በዕለት ሁኔታ መመዝገቢያው ሠነድ ላይ እንዳይመዘግበው ስምምነት መደረጉ ነው የታወቀው።
Negarit Ethiopia: The father, Aboy Sebhat, has a license to Kill; why not the son, right?
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment