Tuesday, January 19, 2010

አልነጋም- ገና ነው!

ዳግማዊ ዳዊት
Ethio_dagmawi@yahoo.com
ጥር 2002 ዓ.ም.

የሰማይ ኮርኔሥ ሆኖ- ማቅ የመሰለ ደመና
ከታችም አውሎ ነፋስ- ፉጨቱን እያሰማ
አቧራውን አሥነስቶ- ዛፍ ቅርንጫፉን እያሾረ
ዛሩ እንደወረደ ባለአውሌ- አለመጠን እያስጨፈረ
አይን ቢወጉ በማያሳይ- ጥቅጥቅ ባለ ጨላማ
ወዴት ነው መድረሻችን- ጉዟችን የሚያቀና?
ትናንት እንዳስቆመን ዝናብ- ሊዘንብ ሰማዩ አግቶ
ወዴት ነው የምንሄደው- በትናንቱ ምን ታይቶ?
ትርምስምሳችን ወጥቶ- ጨቅይቶ ሳለ መንገዱ
ለይምሰል አይሆንምወይ -ደግመን ዛሬ መሄዱ?
ትናንት መካሪ ጠፍቶ- ሌሊቱ ገና እናዳልነጋ
ጉዞው መርዛም-እሾክ በዝቶበት- ስንቱ ነው የተወጋ?
እኔስ አልምክርውም- የዛሬውን መንገድ
እስኪነጋ እቆያለሁ- ካልሆነብኝ የግድ
አልነጋም ገና- ጨለማ ነው ሌሊት
እነሱንም ንገሩዋቸው- መጓዙን ይተውት
ተከታያቸውን በመሉ- የአውሬ ቀለብ አያርጉት።

No comments: